ጦርነትና የስነ-ልቦና ቀዉሶች

ጦርነት እና ሽብርተኝነት በሰው ልጆች የሃይል ሚዛን መዛባት ምክንያት የሚፈጸሙ የኃይል ድርጊቶች ናቸው፡፡ በግጭት እና በጦርነት ጊዜ በህብረተሰቡ ውስጥ የተለያዩ የስነ-ልቦና መቃወሶች እና ምልክቶች መከሰታቸው የሚጠበቅ ነው ፤መገለጫውም ሁለንተናዊ ይሆናል፡፡ በጦርነት ውስጥ በጣም አስከፊ የስሜት ቀውስ ቢከሰትም ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ጫናውን የመቋቋም አቅም ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ውጤቱም በስሜት፣ በአስተሳሰብ እና በስነ-ልቦና የተጎዱ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ይፈጥራል፡፡ ጠባሳውም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ከውስጣቸው በቀላሉ የማይወገድና ጊዜ የማይሽረው ይሆናል፡፡በጦርነት ቀጠና ውስጥ ከሚኖሩ ሶስት ልጆች መካከል አንዱ ለተለያዩ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ለከፍተኛ ጭንቀት፣ ድባቴ እና የድህረ አደጋ ጭንቀት (PTSD) እንዲሁም የነርቭ አስተላላፊ ስርዓቶችን የማቃወስ፣ ፍርሃት፣ መረበሽ፣ ፀብን የመቆጣጠር ችግር (ግልፍተኝነት)፣ በነርቭ አወቃቀር ስርአት ውስጥ (CNS) መዋቅራዊ ለውጦችም ያመጣል፡፡ ስለሆነም በዚህ ወቅት ጦርነቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በቀጥታ ተጠቂና ተሳታፊ ለሆኑ የማህበረስብ ክፍሎች ከማህበራዊ እና ከኢኮኖሚያዊ ድጋፍ በዘለለ የስነ-ልቦና ድጋፍ ጉዳይ ሊታሰብበትና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግዳሮት እንደሆነ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *